ወደ ዕብራውያን

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥
 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ (1: 1-3)

አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። (1:8)

አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ (1: 11)

እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት። (2: 4)

ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። (2:9)

ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና። (2: 10)

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። (2: 15)

ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ (3:1)

ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ (3: 12)

 ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። (4:2)

ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና። እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። (4:10-11)

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤  እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። (4: 12-13)

እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። (4: 14-16)

እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበእግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ (5: 7-8)

ወደ ዕብራውያን መግቢያ
ወደ ዕብራውያን 1: 1-3
ወደ ዕብራውያን 1: 4-14
ወደ ዕብራውያን 2: 1-4
ወደ ዕብራውያን 2: 5-9
ወደ ዕብራውያን 2: 10-13
ወደ ዕብራውያን 2: 14-18
ወደ ዕብራውያን 3: 1-6
ወደ ዕብራውያን 3: 7-19
ወደ ዕብራውያን 4: 1-3
ወደ ዕብራውያን 4: 4-11
ወደ ዕብራውያን 4: 12-13
ወደ ዕብራውያን 4: 14-16
ወደ ዕብራውያን 5: 1-10
ወደ ዕብራውያን 5: 11-14
ወደ ዕብራውያን 6: 1-3
ወደ ዕብራውያን 6: 4 – 6
ወደ ዕብራውያን 6: 7-12
ወደ ዕብራውያን 6: 13-20
ወደ ዕብራውያን 7: 1-10
ወደ ዕብራውያን 7: 11-28
ወደ ዕብራውያን 8: 1-3
ወደ ዕብራውያን 8: 4-13
ወደ ዕብራውያን 9: 1-10
ወደ ዕብራውያን 9: 11-22
ወደ ዕብራውያን 9: 23-28
ወደ ዕብራውያን 10: 1-10
ወደ ዕብራውያን 10: 11-18
ወደ ዕብራውያን 10: 19-23
ወደ ዕብራውያን 10: 24-25
ወደ ዕብራውያን 10: 26-39
ወደ ዕብራውያን 11: 1-3
ወደ ዕብራውያን 11: 4-10
ወደ ዕብራውያን 11: 11-40
ወደ ዕብራውያን 12: 1-3
ወደ ዕብራውያን 12: 4-11
ወደ ዕብራውያን 12: 12-17
ወደ ዕብራውያን 12: 18-29
ወደ ዕብራውያን 13: 1-6
ወደ ዕብራውያን 13: 7-25

Published by Betty & Abera

We’re dedicated to share God’s goodness and mercy through His word!

Leave a comment