የሉቃስ ወንጌል

መግቢያ ይህ ወንጌል የተፃፈው ለአህዛብ ሲሆን በተለይም ለቴዎፍሎስ ነበረ::  ፀሃፊውም እራሱ እስራኤላዊ አይደለም:: በዚህ ወንጌል ውስጥ ብቻ የሚገኙ ታሪኮች አሉ::  ለምሳሌ የመልአክት ዝማሬ እረኞች  ባሉበት ስፍራ መገለጡ ጌታ እየሱስ ሲወለድ: ርኅሩኁ ሳምራዊ ምሳሌ: የጠፋው ልጅ ታሪክ እናም የእየሱስ በልጅነቱ ወደ ቤተመቅደስ መሄዱ:: ይህ ወንጌል  የተፃፈው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን ነው::  በማለት እርሱ የዓይንContinue reading “የሉቃስ ወንጌል”

የዮሐንስ ወንጌል

መግቢያ የዮሐንስ ወንጌል ከሌሎቹ ወንጌሎች ለየት ይላል::  መለየቱም በጣም መንፈሳዊ ነው ማለትም አዲስ ኪዳናዊነቱ በጣም የጎላና የመንፈስ ቅዱስ እርዳታና መገለጥ ያለበት ጥልቅ እይታ ያለው ነው:: አንዳንዶች ስለዚህ ክፍል ሲናገሩ ሌሎቹን አንብቦ የጎደለውን ለመሙላት የተፃፈ ነው ይላሉ::  ከተደረጉት ተአምራት ሰባቱን ብቻ ነው የፃፈልን::  ሌሎቹ የተደረጉትን ነገሮች እንደሪፖርት ሲጽፉ እሱ ግን በእየሱስ አምላክነትና ሰው መሆንን ሊያሳየን ፃፈ::Continue reading “የዮሐንስ ወንጌል”

በክርስቶስ ማን ነኝ?

በክርስቶስ በሰሚያዊው በረከት ሁሉ የባረከኝ በአብም ቀኝ በክርስቶስ ውስጥ የሰወርከኝ ጌታዬ ተባረክ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም መጻተኛና እንግዳ ነኝ ቤቴ በሰማይ ነው:: አሜን! ማንነታችንን እንወቅ፤ እኛ ጌታ እንደሚለን ነን::  እራሳችን ነን ካልነው ሰዎችም ከነገሩን ይልቅ ቃሉ የሚለን ነንና ቃሉ በልባችን ይተከል:: በክርስቶስ ማነኝ? በቀን አንድ የእግዚአብሔር ቃልን ይዘን ስለማንነታችን እናስብ:: ይህንን እውነት እናጥና በልባችንም በቀንምContinue reading “በክርስቶስ ማን ነኝ?”

የይሁዳ መልእክት

መግቢያ:- ይህ በአለአንድ ምዕራፍ ደብዳቤ የተፃፈው በይሁዳ ነው::  ይህ ሰው የጌታ የእየሱስ ወንድም ነው እራሱን ግን የሚጠራው የያዕቆብ ወንድም ብሎ ነው::  ከወንድምነቱ ይልቅ እራሱን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ብሎ ነው የሚጠራው::  የፃፈበትንም ምክንያት ሲናገር እማኞች ሳይሆኑ አማኝ መስለው የሐሰት ትምህርት ከሚያስተምሩ እንዲጠበቁ ለማስጠንቀቅ የተፃፈ ነው:: እግዚአብሔር ለመዳን አንድ ጊዜ በተሰጠው እምነት እንዲፀኑ ይመክራል:: ይሁዳ 1: 1-2Continue reading “የይሁዳ መልእክት”

የዮሐንስ ራእይ

መግቢያ በዚህ መጽሐፍ ብዙ አሳብ አለ ከዚህ መካከልም እንደገባን የምናየው:- 1.  ስለ እየሱስ መገለጥ 2.  የእግዚአብሔርን ፍርድ 3.  ለባርያዎቹ የክርስቶስን ክብር ለማሳየት 4. ወደፊት ሊሆን ያለውን 5.  ስለሐሰተኛው ክርስቶስ እና ሌላም ጥልቅ መጽሐፍ ነው ምክንያቱም ትንቢት ስለሆነ በዚህ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ቃሉን ይግለጥና መረዳትን ይስጠን ይህንን እየሱስን የበለጠ በክብሩ እንወቀው: የማይገባንም ክፍል ቢኖር ስንሄድ ሙሉContinue reading “የዮሐንስ ራእይ”

የያዕቆብ መልእክት

የያዕቆብ መልእክት 1: 1-4 2-3፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት  4፤ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ክርስትና  ፈተና እንዳለው እየሱስ ቁልጭ አድርጎ ነግሮን ነው የሄደው አልዋሸንም::  የሚፈተነውም እምነታችን ነው!  ሲፈተንም የሚያፈራው ትዕግስትን ነው::  በመከራ መታገስ ምክንያቱም ዓለም ባሰመረችልን መንገድ የምንሄድContinue reading “የያዕቆብ መልእክት”

የሐዋርያት ሥራ

የሐዋርያት ሥራ የሚያሳየው እንዴት መንፈስ ቅዱስ እየሱስን እየገለጠውና እያገነነው እንደሆነ ነው:: ቤተክርስትያን በእግዚአብሔር ኃይል እንደተመሰረተችም እናያለን::  ሰው እያየና እየሰማ የእግዚአብሔር መንፈስ በሰው ላይ ወረደ::  ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ድምጽ ከሰማይ መጣ የነበሩበትንም ቤት ሞላው::    2: 4፤ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። 6፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛContinue reading “የሐዋርያት ሥራ”

ወደ ሮሜ ሰዎች

ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (1: 4) ወደ ሮሜ ሰዎች 1: 1-7 ወደ ሮሜ ሰዎች 1: 8-15 ወደ ሮሜ ሰዎች 1: 16-17 ወደ ሮሜ ሰዎች 1: 18-32 ወደ ሮሜ ሰዎች 2: 1-29

ወደ ዕብራውያን

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ (1: 1-3) አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። (1:8) አንተ ግንContinue reading “ወደ ዕብራውያን”

3ኛ የዮሐንስ መልእክት

ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። (2) ወዳጅ ሆይ፥ ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፥ እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤  ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤ (5-6) ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም። (11)