የማቴዎስ ወንጌል

ማቴዎስ 1: 1-17

1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

ማቴዎስ ይህንን ወንጌል የፃፈው ለአይሁዶች ሲሆን በብሉይ ኪዳን የተነገሩትን ትንቢቶች እንዴት እንደተፈጸሙ እያሰመረበት ያልፋል::  ክፍሉንም ሲጀምር የዳዊት ዘር እንደሆነ እንዲያውቁ ትውልዱን አስቀምጧል::

በዚህ የትውልድ ዝርዝር ውስጥ ሴቶችን መቁጠሩ ከመግረምም አልፎ ይደንቃል ነገር ግን ያስገባበት ምክንያት ስለነበረው ነው::  የሴቶቹ ስም ሩት: ትዕማር (ዘፍ 38:25-26): ራኬብ (ረአብ) (ኢያሱ 2:1) እና  የኦርዮን ሚስት (2 ሳሙኤል 11:2-5)::  እነዚህ በኢየሱስ ዘር ግንድ ውስጥ እንዴትገቡ ያስብላል::  አንድዋ ሴተኛ አዳሪና አህዛብ::  ሌላዋ ባልዋ የሞተባትና ሁለተኛ ያገባች አህዛብ:: ትዕማር ባልዋ ሲሞት ከባልዋ አባት ጋር  አታላ የተኛች :  በተፈጸማት ዝሙት የተነሳ  ባልዋ ኦርዮ  የተገደለባት ሴት::  ሁሉም የተሰበረ ህይወት ያላቸው በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት በግልጽ የሚታይ አመጽ ያለባቸውን በግንዱ ላይ አስገባ::  እኛም እራሳችንን እንዳናርቅ የኃጥያተኞች ወዳጅ እየተባለ መጣልን እንጂ ከተቀደሰ ሰውና ዘር ብቻ ልወለድ ለብቻ እነሱን ለዮልኝ ሳይል በኃጥያት የተበከለውን የሰው ልጅ ለመታደግ ንጹ በግ ሆኖ ይህ ሁሉ ኃጥያትና አመጽ ሳይነካው በመንፈስ ቅዱስ ተጸነሰ::  እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ብላ ቃል ስጋ ሆነ!!  አሜን!

አባት ሆይ የሰውን ልጅ እንዴት ባለ ፍቅር ወደድከው?  ምን እንላለን ተመስገን ሳትጠየፍ እራስህን ባዶ አድርገህ መጣህልን!!  ተመስገን!!

ህይወቴ የአንተ ነው!!

ማቴዎስ 1: 18-25

21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”

ዮሴፍ ጻድቅ ሆኖ አርግዛ የተገኘችውን እጮኛውን በአደባባይ ሊገልጣት አልፈለገም::  እውነታውን በእርሱ አንግል ብናየው የተበደለውና የተከዳው እርሱ ሆኖ ሳለ በቀልን አማራጭ አላደረገም::  በስውር ሊተው ነበር ያሰበው::  ጌታ መቼም በቤቱ ሊያድግ ሲመጣ ትክክለኛውን ሰው እንደሚመርጥ የታወቀ ነው::  ለዚህ ሰው መልአኩን ልኮ በህልሙ አጀንዳውን አሳወቀው::  የእግዚአብሔር መንግስት ሚስጥር እኮ ነው የተነገረው ለማን ይህንን ገልጧል ከጥቂቶች በጣት ከሚቆጠሩ በቀር::  የመንግስት ትልቅ  አጀንዳ በሚስጥር ቢነገረን መቼም ሚስጥር መጠበቁን ረስተን ወሬውን ስንት ቦታ እናደርሰዋለን::   ዮሴፍ ግን እንደዛ አልነበረም::  ስንት አይነት ግኑኝነታችን በእኔነት ፈርሶ ይሆን?!  ግንፍል ብሎ ነገሮችን ከማበላሸት መታገስ ይሁንልን:: የክርስቶስ ልብ አለን እንደሚል ሰፊ ልብን ጌታ ያብዛልን::

ይህ ሰው አውጥቶ አውርዶ በተኛበት ለማንም ባላማከረበት የሰማዮ አጀንዳ በመኝታው ተገለጠ::  የአምላኩ የፈጣሪው አደራ ተጣለበትና ፈጣሪውን አቅፎና ተንከባክቦ እንዲያሳድግ ተሰጠው!  ወቸ ጉድ ኢየሱስም የሚያሳድግ: የሚከልለውና የሚንከባከበው የምድር አባት አስፈለገው:: ይህ ሰው ለስራው ብቁና የሰማውን ቶሎ የሚታዘዝ ነው ስለዚህም ማርያምን ወሰዳት::  በመውሰዱም በሰዎች ዘንድ ጻድቅ የነበረው ማንነቱ ወደ መነቀፍ መጣ ዋጋ  ከፈለ  ይህ እርግዝና ከወዴት እንደሆነ የማያውቁ ሁሉ ከባህሉ ውጪ አስረግዟል ብሎ ይነቅፈዋልና::  በባህሉ ይህ እጮኝነትና መተያያ እንጂ የባልና ሚስትን ወግ አይጨምርም ነበረ::  እርሱም የመጣው ይምጣ ብሎ የጌታን አጀንዳ ታዘዘ::  ዛሬም ሰዎች አያስተውሉ ይሆናል የታዘዝነውን ታማኝነታችን ለጌታ ይሁንና እንታዘዝ::  እሺ የሚል እርምጃን ለመውሰድ የተዘጋጀ ማንነት ይሁንልን::

አማኑኤል ተወለደልን ስሙንም ኢየሱስ ብሎ እንደተቀበለው ታዞ ሰየመው::  ሰምቶ መታዘዝ ይብዛልን!

Published by Betty & Abera

We’re dedicated to share God’s goodness and mercy through His word!

Leave a comment